The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ PPPDS/VP- 16FBI/06/10/2012 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2020
Bid Description

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር PPPDS/VP- 16FBI/06/10/2012

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ የቤተ መንግስት አስተዳደር፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ፣ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ የብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን እና የወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ እና የፕሬስ ድርጅት ያገለገሉ 47 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ  በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 001 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ ተጫራቾች መመሪያእና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፣
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ(20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡  ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡  እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡  ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
  8. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122 37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  11. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

 

Bid Attachment

15 11 2012 disposal2.docx

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 28/07/2020
Bid Closing Time 10:00 am
Expected Award Date28/08/2020
Extended To
Reason for extension